ቀጥታ፡

አምስት ህጻናትን በሰላም የተገላገሉት እናት

ሐረር፤ ሚያዝያ 28/2018(ኢዜአ)፦ በሐረር ከተማ በሚገኘው የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ህይወት ፋና ስፔሻላይዝድ አጠቃላይ ሆስፒታል አንዲት እናት አምስት ህጻናትን በሰላም ተገላግለዋል።

በሐረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ ቂሌ ቀበሌ ነዋሪዋ ወይዘሮ በድሪያ አደም የተባሉ የ35 ዓመት እናት ትናንት ከምሸቱ 3: 30 ላይ አምስት ህጻናትን በሰላም መገላገላቸውን የሆስፒታሉ ሀኪም ዶክተር ኦብሳ ሀሰን ተናግረዋል።

የእርግዝና ቆይታቸውን በህይወት ፋና ስፔሻላይዝድ አጠቃላይ ሆስፒታል ክትትል ሲያደርጉ እንደነበርም ገልጸዋል።

ዶክተር ኦብሳ አክለውም፤ ወይዘሮ በድሪያ አራት ወንድና አንድ ሴት ህጻናት በሰላም መገላገላቸውንና ሁሉም ህጻናትና እናትየው በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም