ቀጥታ፡

አርባምንጭ ከተማ ድል ሲቀናው ድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ተጋርተዋል 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 27/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርባምንጭ ከተማ መቀሌ 70 እንደርታን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አብዱል ራህማን እና አሸናፊ ፊዳ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በሊጉ አምስተኛ ድሉን ያስመዘገበው አርባምንጭ ከተማ በ28 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ይዟል። 

ላለመውረድ በሚያደርገው ትግል ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።

በውድድር ዓመቱ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቀሌ 70 እንደርታ በ30 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። 

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ድሬዳዋ ከተማ በ34 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት አራት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።

ኢትዮጵያ ቡና በ42 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም