ቀጥታ፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 27/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ24ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ቦሌ ክፍለ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳግማዊት ሰሎሞን በ22ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች።

የኢትዮ ኤሌክትሪኳ ማህሌት ምትኩ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።

በሊጉ 20ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ63 ነጥብ ከመሪው ንግድ ባንክ ጋር በነጥብ እኩል የሆነ ሲሆን በግብ ክፍያ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

የዋንጫ ተፎካካሪ የሆኑት ሁለቱ ቡድኖች በ25ኛ ሳምንት እርስ በእርስ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቦሌ ክፍለ ከተማ በ40 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮ ኤሌክትሪኳ ዳግማዊት ሰሎሞን በሊጉ ያስቆጠራቻቸውን ጎሎች ወደ 24 ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት መሪነቷን አጠናክራለች።

ዛሬ በተደረገ የ24ኛ ሳምንት ጨዋታ አዲስ አበባ ከተማ እና አዳማ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይቷል።

ጨዋታዎቹን ተከትሎ የ24ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም