ቀጥታ፡

ለዘላቂ ሰላምና ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት በመትጋት ድህነትን መርታት አለብን - አባት አርበኞች

ደብረ ብርሃን፤ ሚያዝያ 27 (ኢዜአ)፡- ለልማት፣ ለዘላቂ ሰላምና ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት በመትጋት ድህነትን መርታት አለብን ሲሉ አባት አርበኞች ተናገሩ።

85ኛው የድል በዓል በደብረ ብርሃን ከተማ ተከብሯል።


 

በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ዋና ፀሐፊ ዮሐንስ ተሰማ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ አሁን ላይ ድህነትን ማሸነፍ የሁላችንም የጋራ አጀንዳ ሆኖ መቀጠል አለበት።


 

ተተኪ አርበኛ አባተ ኃይሌ በበኩላቸው፤ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ሀገርን ከድህነት ለማስወጣት መልካም ጅምሮች መሆናቸውን ገልጸው፤ ለልማት፣ ለሰላምና አብሮነት በመሥራት ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነት በመትጋት ድህነትን መርታት አለብን ሲሉ ተናግረዋል። 


 

አያቶቻችን ሀገርን ከጠላት በመጠበቅ በጀግንነት ብዙ መስዋዕትነት መክፈላቸውን ያወሱት በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአጼ ዘርዓ ያዕቆብ የባህል ታሪክና ቋንቋ ልማት ማዕከል ዳይሬክተር ዘመነወርቅ ዮሐንስ (ዶ/ር)፤ የዚህ ትውልድ ዋነኛ ዓላማ ደግሞ ሀገርን ከድህነት ማውጣት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የአሁኑ ትውልድ ትልቁ አደራና ኃላፊነትም በተደመረ ዐቅም ድህነትን ድል በማድረግ ለሁላችንም የምትመች ጠንካራ ሀገር መገንባት ሊሆን ይገባል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም