የቀድሞው የኢቢሲ ጋዜጠኛ አብዲ ከማል ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ - ኢዜአ አማርኛ
የቀድሞው የኢቢሲ ጋዜጠኛ አብዲ ከማል ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 27/2018 (ኢዜአ) ፦የቀድሞው የኢቢሲ ጋዜጠኛ አብዲ ከማል ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
ስርአተ ቀብሩም በዛሬው ዕለት ተፈፅሟል።
ጋዜጠኛ አብዲ ከማል ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በተለያዩ የሥራ መደቦች ላይ አገልግሏል።
ጋዜጠኛው በቆይታው ከሪፖርተርነት እስከ ዋና አዘጋጅነት በመድረስ በሙያው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ጋዜጠኛ አብዲ ከማል ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ጠዋት ህይወቱ ያለፈ ሲሆን የቀብር ሥነ-ሥርዓቱም በኮልፌ የሙስሊሞች መቃብር መፈጸሙን ኢቢሲ ዘግቧል።
ጋዜጠኛ አብዲ ከማል ባለትዳር እና የ3 ልጆች አባት ነበር።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትም በጋዜጠኛ አብዲ ከማል ህልፈት የተሰማውን ሀዘን በመግለጽ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለሙያ አጋሮቹ መፅናናትን ይመኛል።