ቀጥታ፡

አዲስ አበባ ከተማ እና አዳማ ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 27/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት አዲስ አበባ ከተማ እና አዳማ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተካሄዷል።

ውጤቱን ተከትሎ አዲስ አበባ ከተማ በ12 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

አዲስ አበባ ከተማ ከመውረድ ለመትረፍ ቀሪ ሁለት የሊግ ጨዋታዎቹን የማሸነፍ ግዴታ የገባ ሲሆን 12ኛ ደረጃ ላይ ያለውን የይርጋጨፌ ቡና ነጥብ መጣልም ይጠብቃል።

አዳማ ከተማ በ22 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም