ቀጥታ፡

በከተማዋ ሃገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የልማት ተግባራት በውጤታማነት እየተከናወኑ ነው

ባህርዳር ፤ ሚያዝያ 27/2018 (ኢዜአ)፦ብልፅግና ፓርቲ በባህር ዳር ከተማ ሃገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የልማት ተግባራትን በውጤታማነት እያከናወነ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው አመለከቱ።

ብልፅግና ፓርቲ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የጎዳና ላይ የምረጡኝ ቅስቀሳውን በባህር ዳር ከተማ አካሄዷል።


 

በምረጡኝ ቅስቀሳ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እንዳሉት፤ ብልፅግና ፓርቲ ሃገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የልማት ተግባራትን በውጤታማነት እያከናወነ ነው። 

በዚህም ሁለንተናዊ ብልፅግናን በማረጋገጥ ረገድ እየተከናወኑ ያሉ ሁለንተናዊ ተግባራት የሃገሪቱን ዘላቂ ለውጥ የሚያረጋግጡ መሆናቸውን አመልክተዋል። 

የኢትዮጵያ ብልፅግና አይቀሬ መሆኑን በተከናወኑ ተግባራት ማረጋገጥ ይቻላል ያሉት አቶ ጎሹ፤ ፓርቲውም ለኢትዮጵያ ነፃነት፣ እድገትና ብልፅግና እየተጋ ነው ብለዋል። 

በዚህም የብልፅግና ትክክለኛ ማሳያ የሆኑ ተግባራት በባህር ዳር ከተማ መከናወናቸውን ጠቅሰው፤ ከተማዋ በብልፅግና ዘመን እንደ አዲስ ታድሳለች ብለዋል።

በባህር ዳር በልዩ ትኩረት የተከናወነው የኮሪደር ልማት ስራ ከተማዋን የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ከተማ በማድረግ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት የማሳደግ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። 

በሃገር አቀፍ ደረጃም ሆነ በከተማው የተጀመሩና እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠልም በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ የቀረቡ እጩዎችን በመምረጥ አጋርነቱን ሊያረጋግጥ ይገባል ሲሉም አመልክተዋል። 


 

የባህር ዳር ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሞላ ሁሴን በበኩላቸው፤ ብልፅግና ለትውልድ የሚተርፉ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በውጤታማነት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። 

በዚህም በከተማ አስተዳደሩ የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማት ስራዎችን በማከናወን ለብልፅግና ጉዞ እውን መሆን ማሳያ ስራዎችን መስራቱን አስረድተዋል። 

ብልፅግና በመደመር እሳቤ እየተመራ ለዘላቂ ልማት፣ ሰላም እና አንድነት ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል። 

የስንዴ ነዶ የአንድነትና የመተባበር ምሳሌ እንደሆነ ጠቅሰው፤ በከተማዋ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ወደ ላቀ ከፍታ ለማሳደግ ብልፅግናን ይምረጡ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም