ቀጥታ፡

ማን ለፍጻሜው ያልፋል? አርሰናል ወይንስ አትሌቲኮ ማድሪድ? 

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 27/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አርሰናል ከአትሌቲኮ ማድሪድ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ። 

የሁለቱ ክለቦች ጨዋታው ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል።

ቡድኖቹ ባለፈው ሳምንት ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይተዋል። 

ቪክቶ ዮኮሬስ ለአርሰናል፣ ሁሊያን አልቫሬዝ በፍጹም ቅጣት ምት ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጠንካራ አቋም እያሳየ ያለው አርሰናል ጨዋታውን አሸንፎ ወደ ፍጻሜ የማለፍ የቅድሚያ ግምት ተሰጥቶታል።

አትሌቲኮ ማድሪድ በጨዋታው ጠንካራ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

አርሰናል በሻምፒዮንስ ሊጉ ለሁለተኛ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ ለአራተኛ ጊዜ ለፍጻሜ ለማለፍ ይጫወታሉ።

ሁለቱም ቡድኖች የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አንስተው አያውቁም።

የ42 ዓመቱ ጀርመናዊ  ዳንኤል ሲበርት ጨዋታውን በዋና ዳኝነት እንዲመሩ ተመድበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም