ቀጥታ፡

ማንችስተር ሲቲ ከኤቨርተን ጋር አቻ በመውጣት ወሳኝ ነጥብ ጣለ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 26/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 35ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኤቨርተን እና ማንችስተር ሲቲ ሶስት አቻ ተለያይተዋል።

 

ማምሻውን በሂል ዲኪንሰን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቲዬርኖ ባሪ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ጃክ ኦብራያን ቀሪዋን ጎል ለኤቨርተን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ጀረሚ ዶኩ ሁለት ግቦቹን ሲያስቆጥር አርሊንግ ሃላንድ ቀሪዋን ጎል ለማንችስተር ሲቲ ከመረብ ጋር አገናኝቷል።

ዶኩ በ97ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል ሲቲን አቻ አድርጓል።

 

ማንችስተር ሲቲ በመጀመሪያው አጋማሽ 1 ለ 0 እየመራ ቢወጣም ከእረፍት መልስ ኤቨርተን ያሳየው ጠንካራ ብቃት ከሲቲ የተከላካይ ክፍል ስህተቶች ጋር ተዳምሮ አቻ ወጥቷል።

ማንችስተር ሲቲ በ71 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ሲቲ በእጁ ያለውን ዋንጫ የመወሰን እድል ያጣ ሲሆን ከመሪው አርሰናል ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት አምስት ሆኗል።

አርሰናል ዋንጫውን በራሱ የመወሰን እድሉን በእጁ አስገብቷል።

ኤቨርተን በ48 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም