ቀጥታ፡

በሀረሪ ክልል ለቱሪዝም ዘርፉ የተሰጠው ትኩረት አበረታች ውጤት የታየበት ነው

አዲስ አበባ ፤ ሚያዝያ 26/2018(ኢዜአ)፦ በሀረሪ ክልል ለቱሪዝም ዘርፉ የተሰጠው ትኩረት አበረታች ውጤት የተመዘገበበት ነው ሲሉ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ገለጹ።

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር የተመራው የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች የልዑካን ቡድን በሀረር ኢኮ ፓርክ የጅብ ትርኢትን ተመልክተዋል።


 

ከንቲባው በጉብኝታቸው ላይ እንደተናገሩት በክልሉ መሰል የቱሪዝም መስህቦችን ለማስፋፋት የተደረገው ጥረት አበረታች ውጤት የታየበት ነው።

በክልሉ የተገነባው የጅብ ትርዒት ማሳያ ፓርክም ለቱሪስቶች ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል ያሉት ከንቲባው ይህም የቱሪዝም ዘርፉን በማጎልበት ከተማዋን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል።


 

የሀረር ከተማን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችም ውጤታማና አበረታች መሆናቸውን እንደተመለከቱ ገልጸዋል።

በጉብኝቱ ላይ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የሀረሪ ክልል እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም