ቀጥታ፡

ሃዋሳ ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 26/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ24ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሃዋሳ ከተማ ይርጋጨፌ ቡናን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቅድስት ቴቃ እና የምስራች ላቀው ግቦቹን አስቆጥረዋል።

የሃዋሳ ከተማዋ ለምለም አስታጥቄ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።

ውጤቱን ተከትሎ ሃዋሳ ከተማ በ49 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል።

ይርጋጨፌ ቡና በ17 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም