በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ድቻ ሀዲያ ሆሳዕናን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ድቻ ሀዲያ ሆሳዕናን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 26/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ሀዲያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መልካሙ ቦጋለ በ40ኛው ደቂቃ ጎሉን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ወላይታ ድቻ በ38 ነጥብ ከነበረበት 11ኛ ደረጃ ወደ 8ኛ ከፍ ብሏል።
ሀዲያ ሆሳዕና በ35 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።