ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2026 የAPEX መንገደኞች ምርጫ 'በአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ' ሽልማትን አሸንፏል

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 26/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2026 የAPEX መንገደኞች ምርጫ 'በአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ' ሽልማትን አሸንፏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2026 የAPEX መንገደኞች ምርጫ 'በአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ' (Best Airline in Africa) ሽልማትን በማሸነፍ የአቪዬሽን መሪነቱን አረጋገጠ።

ይህ እውቅና አየር መንገዱ በመላው ዓለም በሚያደርጋቸው በረራዎች ቀልጣፋ፣ ምቹ እና አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሲሆን፤ ሽልማቱም ሙሉ በሙሉ በመንገደኞች እውነተኛ የጉዞ ተሞክሮ በተሰጠ ድምፅ አማካኝነት ነው።

አየር መንገዱ 'ራዕይ 2040' በተሰኘው ስትራቴጂካዊ ዕቅዱ በዓለም ካሉ 20 ቀዳሚ የአቪዬሽን ግሩፖች አንዱ ለመሆን እየሠራ ሲሆን፣ በቶጎ፣ ማላዊ፣ ዛምቢያ እና ኮንጎ ከሚገኙ አየር መንገዶች ጋር በመተባበር የበርካታ ማዕከላት (multi-hub) ስትራቴጂን በመተግበር ላይ እንደሚገኝም ታውቋል።

#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም