ቀጥታ፡

ማንችስተር ሲቲ ከኤቨርተን ጋር ይጫወታል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 26/2018 (ኢዜአ)፦  የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኛ ሳምንት 35ተኛ  ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል።

በዕለቱ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ምሽት አራት ሰዓት ላይ ኤቨርተን ከማንችስተር ሲቲ በሂል ዲኪንሰን ስታዲየም ይጫወታሉ።

ኤቨርተን በ47 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል። ማንችስተር ሲቲ በ70 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ከድል የራቀው ኤቨርተን ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል። ቡድኑ ሶስት ነጥብ ካገኘ በአውሮፓ መድረክ የመሳተፍ ተስፋውን ይበልጥ ያለመልማል።

በጥሩ ወቅታዊ ብቃት ላይ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ ከአርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት ዝቅ ለማድረግ እና በዋንጫው ፉክክር ለመቆየት ይፋለማል።

 

በሌላኛው መርሐ ግብር ቼልሲ ከኖቲንግሃም ፎረስት በስታምፎርድ ብሪጅ ከቀኑ ስታዲየም ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

ቼልሲ በ48 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ተጋጣሚው ኖቲንግሃም ፎረስት በ39 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል።

ባለሜዳው ቼልሲ ባለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዷል። ይህን ተከትሎም ሊያም ሮሲኒየር ከአሰልጣኝነታቸው ተሰናብተዋል።

ቼልሲ በጊዜያዊው አሰልጣኝ ካሉም ማክፋርሌን እየተመራ የዛሬውን ጨዋታ ያደርጋል።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ በሂሳባዊ ስሌት ወደ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመግባት ያለውን የእድል በር እንዳይዘጋ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ግድ ይለዋል።

በ34ኛው ሳምንት ሰንደርላንድን 5 ለ 0 የረታው ኖቲንግሃም ፎረስት ላለመውረድ በሚያደርገው ትግል ጠንካራ ፍልሚያ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም