ቀጥታ፡

ኢንተር ሚላን የሴሪአውን ዋንጫ ለ21ኛ ጊዜ ማንሳቱን አረጋገጠ 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በጣልያን ሴሪአ የ35ኛ ሳምንት ጨዋታ ኢንተር ሚላን ፓርማን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በሳንሲሮ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ማርከስ ቱራም እና ኤነሪክ ሚኪታሪያን ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በሊጉ 26ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢንተር ሚላን በ82 ነጥብ ሶስት ጨዋታዎች እየቀየሩት የሴሪአው ዋንጫ ባለቤት መሆኑን አረጋግጧል።

ኢንተር የሊጉ ዋንጫ ሲያነሳ የአሁኑ ለ21ኛ ጊዜ ነው።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 13ኛ ሽንፈቱን የቀመሰው ፓርማ በ42 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም