የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት - ኢዜአ አማርኛ
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት
ባሕር ዳር ጥንታዊነትን ከዘመናዊነት።
በዚህ አካባቢ ታሪክ መጻፍ ከጀመረ መቶዎች ዓመታት አልፈዋል። ዛሬ ደግሞ ታሪክ ወደፊት እየሄደ ነው።
የባሕር ዳር የኢንዱስትሪ፣ የመዝናኛ እና የመሠረተ ልማት ለውጦች ታሪክን ወደ ነገ እየወሰዱት ነው።
ዛሬ ከባለ ሀብቶች እና ከአባ ገዳዎች ጋር ሆነን የባሕር ዳርን ስታዲየም፣ አዲሱን የአውሮፕላን ተርሚናል፣ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የኮሪደር ልማትን ጎብኝተናል።
በጉብኝታችን መንገዳችን ትክክል፣ መዳረሻችን አይቀሬ መሆኑን አረጋግጠናል። ባሕር ዳር የሥልጣኔ ዳር ሳትሆን ዕረፍት አይኖረንም።