ቀጥታ፡

ቶተንሃም ሆትስፐርስ አስቶንቪላን በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና ወጣ 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ35 ሳምንት መርሐ ግብር ቶተንሃም ሆትስፐርስ አስቶንቪላን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በቪላ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኮኖር ጋላገር እና ሪቻርልሰን ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ኤሚሊያኖ ቡንዲያ ለአስቶንቪላ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።

በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ37 ነጥብ ደረጃውን ከ18ኛ ወደ 17ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል። በሊጉም ዘጠነኛ ላይ አሳክቷል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አስቶንቪላ በ58 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

ቡድኑ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመግባት በሚያደርገው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ አጥቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም