በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተመርቆ የተከፈተው ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት… - ኢዜአ አማርኛ
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተመርቆ የተከፈተው ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት…
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርትን መነሻ በማድረግ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል ሆኖ በግል ኢንቨስትመንት በባህር ዳር ከተማ የተገነባውን የፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል፡፡
ስለፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት በጥቂቱ፦
✅በባህር ዳር ከተማ በጣና ሐይቅ ደቡባዊ ዳርቻ ላይ ተገንብቷል፤
✅በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ገበታ ለሀገር" እቅድ መሰረት በሐይቁ ሌላኛው አቅጣጫ ከሚገኘው የጎርጎራ ብርሃን (ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት) ጋር በመቀናጀት የጣናን የቱሪዝም ቀጣና ለማነቃቃት የታለመ ነው፤
✅ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጎበታል፤
✅ በሁለት ዓመት ከስድስት ወር (30 ወራት) ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለምረቃ በቅቷል፤
✅በሀገር በቀሉ ባለሀብት በአቶ ካሳሁን ምስጋናው (የቤአኢካ ንግድና ኢንቨስትመንት መሥራች) አማካኝነት በግል ኢንቨስትመንት የተገነባ ነው፤
✅ሪዞርቱ አዲስ በተቋቋመው ሮዳ ሆስፒታሊቲ ግሩፕ ስር ይተዳደራል፤
✅ሮዳ ሆስፒታሊቲ ግሩፕ ይህንን አዲስ ሪዞርት እና የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርትን በአንድ ላይ በማስተዳደር የቀጣናውን የሆስፒታሊቲ አገልግሎት ይመራል፤
✅ኢኮ-ሪዞርቱ፦ የተፈጥሮ አካባቢን በጠበቀ መልኩ የተገነባ የቱሪስት መዳረሻ ነው፤
✅በግል ኢንቨስትመንት ቢገነባም፣ በመንግሥት የገበታ ለሀገር ማዕቀፍ ኢኒሼቲቮች ውስጥ ተካትቶ የተመራና ትኩረት የተሰጠው ፕሮጀክት ነው፤
✅ሪዞርቱ ለአማራ ክልልም ሆነ ለሀገሪቱ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ አዲስ የገቢና የሥራ ዕድል ምንጭ እንደሚሆንም ይጠበቃል።