መቻል በድል ጉዞው ቀጥሏል - ኢዜአ አማርኛ
መቻል በድል ጉዞው ቀጥሏል
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት መቻል ባህር ዳር ከተማን 3 ለ 2 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቱሪስት ለማ፣ ትዕግሥት ወርቁ እና መዲና አወል ለመቻል ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ሳሮን ሰመረ እና ማናዩሽ ተስፋዬ ለባህር ዳር ከተማ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
የመቻሏ ቱሪስት ለማ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
በሊጉ ተከታታይ ሶስተኛ ድሉን ያስመዘገበው መቻል በ54 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። በውድድር ዓመቱ 16ኛ ድሉን አሳክቷል።
በሊጉ 17ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ባህር ዳር ከተማ በ19 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ዛሬ አስቀድመው በተደረጉ የ24ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ሸገር አርባምንጭ ከተማን 4 ለ 0፣ ሲዳማ ቡና ልደታ ክፍለ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፈዋል።