ማንችስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን 3 ለ2 በሆነ ውጤት አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን 3 ለ2 በሆነ ውጤት አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በተደረገው ተጠባቂ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን 3 ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የቀያይ ሰይጣኖቹን የማሸነፊያ ግቦች ኩንያ ፤ ቤንጃሚን ሴስኮ እና ኮቢ ማይኖ አስቆጥረዋል።
ለሊቨርፑል ግቦችን ስቦዝላይ እና ኮዲ ጋክፖ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ ማሸነፉን ተከትሎ ወደ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ መመለሱን አረጋግጧል።
ማንችስተር ዩናይትድ በዚህ አመት ሊቨርፑልን በሁለቱም ዙር ጨዋታዎች ማሸነፍ ችሏል።
ማንችስተር ዩናይትድ በ64 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ያስጠበቀ ሲሆን ሊቨርፑል በ58 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ሁለቱ ክለቦች እስከ አሁን በሁሉም ውድድሮች 245 ጊዜ ተገናኝተው ማንችስተር ዩናይትድ 93 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ሲይዝ ሊቨርፑል 82 ጊዜ አሸንፏል።70 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ ማሸነፉን ተከትሎ በቀጣይ ወደ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር መመለሱንም አረጋግጧል።