ቀጥታ፡

‎በዘንድሮው “ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖ ላይ የሀገራዊ ርዕያችንን ተጨባጭ ስኬት መመልከት ትልቅ ክብር ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

‎አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦በዘንድሮው “ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖ ላይ የሀገራዊ ርዕያችንን ተጨባጭ ስኬት መመልከት ትልቅ ክብር ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአራት ዓመታት ተከታታይ ጥረት እና የሚጨበጥ ውጤት! በሚል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ‎በዘንድሮው “ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖ ላይ የሀገራዊ ርዕያችንን ተጨባጭ ስኬት መመልከት ትልቅ ክብር ነው ብለዋል።


 

በውጤት ተኮር አመራራችን ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ የኢንዱስትሪ መስፋፋት ተንጸባርቋል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ይኸውም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን አማካይ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ በማድረግ፣ ባለፉት አራት አመታት ከ2,800 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ የተቻለ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

እንዲሁም በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ በሀገር ውስጥ ተኪ ምርት ከ4.85 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ በማዳን መረጋገጡን አመላክተዋል።


 

ኤክስፖው ከመላው የሀገሪቱ የተወጣጡ ንቁ አምራቾችን እና ስታርትአፖችን በጨመረ ዐቅም በአንድነት ማሰባሰቡን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‎በጋራ በመሆን ይህንን ጠንካራ መነቃቃት በማስቀጠል፣ ለሚመጣው ትውልድ ጸኑ፣ በኢንዱስትሪ የበለጸገች እና ራሷን የቻለች ኢትዮጵያን እንገነባለን በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም