ቀጥታ፡

ሕክምና ኮሌጁ በተለያዩ የሕክምና ሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 556 ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በተለያዩ የሕክምና ሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 556 ተማሪዎች ዛሬ አስመረቀ። 

የኮሌጁ ተመራቂዎች በሕክምና፣ በስፔሻላይዜሽንና በተለያዩ የጤና ሳይንስ ዘርፎች የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 204ቱ ሴቶች ሲሆኑ፤ 14ቱ ደግሞ ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የመጡ መሆናቸው ታውቋል። 


 

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ፕሮቮስት ዶክተር ሙሉቀን ተስፋዬ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ኮሌጁ ባለፉት 13 ዓመታት በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ያሉ ባለሙያዎችን አፍርቷል። 

ተቋሙ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርትና ሥልጠና በመስጠት ረገድ ውጤታማ ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱንም አመልክተዋል።


 

በአሁኑ ወቅት በኮሌጁ የሰለጠኑ ባለሙያዎች በተለያዩ የጤና ተቋማት ተሰማርተው የኅብረተሰቡን የጤና ችግር በማቃለል ረገድ ትልቅ ሚና እየተወጡ እንደሚገኙ ዶክተር ሙሉቀን አስታውቀዋል። 

የኮሌጁ የዛሬው የምረቃ መርሐ-ግብር  ለ13ኛ ጊዜ መሆኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም