በሶማሌ ክልል በለውጡ ዓመታት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል - ኢዜአ አማርኛ
በሶማሌ ክልል በለውጡ ዓመታት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል
ጎዴ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል በለውጡ ዓመታት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን በብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ እና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብዱራህማን አህመድ ተናገሩ።
የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሃግብር በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን፣ ጎዴ ከተማ አካሄዷል።
በፓርቲው የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ እና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብዱራህማን አህመድ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት ብልጽግና ፓርቲ ባለፋት የለውጥ ዓመታት በሀገረ መንግሥት ግንባታ የተለያዩ ስኬቶች አስመዝግቧል።
ፓርቲው የሀገሪቱን ዜጎች በሁሉም ዘርፎች የሚያሳትፍ አካታችና አሳታፊ ፓርቲ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
በተለይም በሶማሌ ክልል በለውጡ ዓመታት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።
ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ እያከናወነ በሚገኘው የልማት ሥራዎች አበረታች ለውጦች ማምጣታቸውን ገልጸው በክልሉ የተጀመረው ልማት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
በምረጡኝ ቅስቀሳው ብልጽግና ፓርቲን በክልልና በፌዴራል ምክር ቤት የሚወክሉ እጩዎች ተገኝተዋል።