ቀጥታ፡

‎ኢትዮጵያ በምናብ የምትሳል ህልም ብቻ ሳትሆን በተግባር የምትገነባ እውነታ ናት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 22/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በምናብ የምትሳል ህልም ብቻ ሳትሆን በተግባር የምትገነባ እውነታ ናት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የአራዳ ፓርክ አዲስ አበባን ለመለወጥ ያለውን ርዕይ በተግባር ያሳየ አንዱ ስራ መሆኑን ገልጸዋል።


 

ቀደም ሲል ተዘንግቶና ለአደጋ ተጋልጦ የነበረው የአራዳ አካባቢ፣ ዛሬ ተመልሶ ተገንብቶ አስደናቂ የከተማ አካል መሆን መቻሉን አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ በምናብ የምትሳል ህልም ብቻ ሳትሆን በተግባር የምትገነባ እውነታ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።


 

ጤናማ፣ ጽኑ፣ ለመጭው ትውልድ ተስፋን ከተጨባጭ ሀብት ጋር የምትሰጥ፣ በአፍሪካ መሪ፣ በዓለም መድረክ ደግሞ ተወዳዳሪ የሆነች ሀገር እየተገነባች እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።

ይህንን ተስፋ ወደ እውነታ የመለወጥ ተግባር በየቀኑ እንደሚቀጥልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም