ቀጥታ፡

አርባምንጭ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለ ግብ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 22/2018 (ኢዜአ):- የአርባምንጭ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ29ኛ ሳምንት ጨዋታ ምንም ግብ ሳይቆጠርበት በአቻ ውጤት ተጠናቋል። 

ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሄዷል።

ውጤቱን ተከትሎ አርባምንጭ ከተማ በ25 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ይዟል። ቡድኑ ባለፉት አራት ጨዋታዎች አላሸነፈም።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ35 ነጥብ ደረጃውን ከ13ኛ ወደ 11ኛ ከፍ ያደረገ ቢሆን ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም