ነገሌ አርሲ እና ፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ነገሌ አርሲ እና ፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ነገሌ አርሲ እና ፋሲል ከነማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታው በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል።
ውጤቱን ተከትሎ አዲስ አዳጊው ነገሌ አርሲ በ45 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት አራት ጨዋታዎች አላሸነፈም።
ፋሲል ከነማ በ43 ነጥብ ደረጃውን ከስድስተኛ ወደ አምስተኛ ከፍ አድርጓል። ቡድኑ ባለፉት የሊግ ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።