ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሪነቱን ያጠናከረበት ድል አስመዘገበ 

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ከተማን 4 ለ 0 ረቷል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ረድኤት አስረሳኸኝ ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር እሙሽ ዳንኤል እና መሳይ ተመስገን ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ ሰናይት ቦጋለ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።

በሊጉ 19ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ60 ነጥብ ተመሳሳይ ነጥብ ያለውን ኢትዮ ኤሌክትሪክን በግብ ክፍያ በልጦ መሪነቱን አጠናክሯል።

የሁለቱ ቡድኖች የዋንጫ ፉክክር አጓጊ ሆኗል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 18ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አበባ ከተማ በ11 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

ዛሬ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ኢትዮ ኤሌክትሪክ ይርጋጨፌ ቡናን 2 ለ 1፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 5 ለ 1 አሸንፈዋል።

ጨዋታዎቹን ተከትሎ 23ኛ ሳምንት ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም