ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ይርጋጨፌ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ገብርኤላ አበበ እና ብርሃን ኃይለስላሴ የማሸነፊያ ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
አዳነች አስፋው የይርጋጨፌ ቡናን ብቸኛ ግብ አስቆጥራለች።
ግብ ያስቆጠረችው ገብርኤላ አበበ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
በሊጉ 19ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ60 ነጥብ የሊጉን መሪነት በጊዜያዊነት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተረክቧል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 14ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ይርጋጨፌ ቡና በ17 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።