መቀሌ 70 እንደርታ እና ሀድያ ሆሳዕና አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
መቀሌ 70 እንደርታ እና ሀድያ ሆሳዕና አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በመቀሌ 70 እንደርታ እና በሀዲያ ሆሳዕና መካከል የተደረገው የሊጉ 29ኛ ሳምንት ፍልሚያ በአንድ አቻ ውጤት ተጠናቋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኬኔዲ ገብረጻዲቅ በ49ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ግብ መቀሌ 70 እንደርታን መሪ አድርጓል።
መቀሌ 70 እንደርታ ጨዋታውን በድል ያጠናቅቃል ተብሎ ቢጠበቅም፣ በጭማሪ ሰዓት 97ኛው ደቂቃ ፀጋዓብ ግዛው ከመረብ ጋር ያገናኛት ጎል ሀዲያ ሆሳዕና ነጥብ ተጋርቶ እንዲወጣ አስችላለች።
የሀዲያ ሆሳዕና የተከላካይ መስመር ተጫዋቾች የሆኑት ዳግም ወንድሙ እና ሄኖክ አርፊጮ መደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በጭማሪ ሰዓት በሁለተኛ ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብተዋል።
ውጤቱን ተከትሎ መቀሌ 70 እንደርታ በ30 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት በሚያደርገው ትግል ወሳኝ ሶስት ነጥብ ጥሏል።
ሀዲያ ሆሳዕና በ35 ነጥብ ከነበረበት 14ኛ ደረጃ ወደ 12ኛ ከፍ ብሏል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።