ቀጥታ፡

ቦሌ ክፍለ ከተማ በድል ጉዞው ቀጥሏል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ቦሌ ክፍለ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 5 ለ 1 ረቷል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ምህረት አየለ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርታለች።

ሜላት ጌታቸው እና ትዕግስት ዮሐንስ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ዝናሽ ሰሎሞን የድሬዳዋ ከተማን ብቸኛ ግብ አስቆጥራለች።

ሀትሪክ የሰራችው ምህረት አየለ ኮከብ ተጫዋች ሆና ተመርጣለች።

በሊጉ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ቦሌ ክፍለ ከተማ በ40 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል። በውድድር ዓመቱም 11ኛ ድሉን አግኝቷል።

በሊጉ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በ24 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም