ቀጥታ፡

በምዕራብ ጉጂ ዞን ከ396 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል

ቡሌ ሆራ፤ ሚያዝያ 22/2018 (ኢዜአ)፡- በተያዘው የበልግ ወቅት ከ396 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የምዕራብ ጉጂ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ገለጸ፡፡

387 ሺህ 954 ሄክታር መሬት በበልግ እርሻ ለማልማት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን በጽሕፈት ቤቱ የሰብል ልማትና ጥበቃ ቡድን መሪ ታሪኩ ብዙአየሁ ለኢዜአ ተናግረዋል።


 

በአሁኑ ወቅትም በልግ አብቃይ በሆኑ ወረዳዎች 396 ሺህ 594 ሄክታር በተለያዩ ሰብሎች በማልማት፤ ከዕቅድ በላይ ስኬታማ ሥራዎች ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል።

በበልግ ከለማውም ከ9 ሚሊየን 100 ሺህ ኩንታል በላይ አጠቃላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል ብለዋል።

122 ሺህ 981 ኩንታል ማዳበሪያና 133 ሺህ 240 ኩንታል ምርጥ ዘር ጥቅም ላይ መዋሉንም አረጋግጠዋል።

በዞኑ የሚመረቱ ዋና ዋና የሰብል ዓይነቶችም፤ ስንዴ፣ ጤፍ፣ በቆሎ፣ ቦሎቄና ሌሎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በትራክተር የማረስ፣ የመስመርና የኩታ ገጠም የተሻሻሉ የግብርና አሠራሮች መተግበራቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

በበልግ አዝመራ የሰብል ልማት 294 ሺህ 360 አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች መሳተፋቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም