ቀጥታ፡

በአማራ ክልል እስካሁን ከበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱ ከ9 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ተሰብስቧል

ባሕር ዳር፤ ሚያዝያ 22/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በበጋ መስኖ ከለማው የስንዴ ማሳ ከዘጠኝ ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።


 

‎‎በቢሮው የመስኖ ሰብል አግሮኖሚ ባለሙያ ንጋቴ ዓለማየሁ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ ‎በክልሉ በዘንድሮው የበጋ ወራት 319 ሺህ 547 ሄክታር መሬት በመስኖ ስንዴ ማልማት ተችሏል።

ከዚህ ውስጥም በ274 ሺህ 472 ሄክታር መሬት ላይ ቀድሞ የደረሰውን የስንዴ ሰብል በኮምባይነር ጭምር ታግዞ በመሰብሰብ ከዘጠኝ ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ማግኘት መቻሉን ተናግረዋል።




‎ቀሪውን በሁለት ሳምንታት ሰብስቦና ወቅቶ ወደ ጎተራ ለማስገባት ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።

‎ከቤት ፍጆታ የተረፈውን የስንዴ ምርትም ለአካባቢው የዱቄት ፋብሪካዎች እና ለገበያ ለማቅረብ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም