ቀጥታ፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ከነገ ጀምሮ ይሰጣል

ጂንካ፤ ሚያዝያ 22/2018 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከነገ ጀምሮ ለ5ኛ ዙር የተቀናጀ የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) መከላከያ ክትባት በዘመቻ መልክ እንደሚሰጥ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ እንዳሻው ሽብሩ ገለጹ።

የፖሊዮ ክትባቱ ከነገ ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት በሁሉም መዋቅሮች እንደሚሰጥ ኃላፊው ለኢዜአ ተናግረዋል።

ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ሕጻናት ክትባቱን ይወስዳሉ ብለዋል።


 

ቤት ለቤት በመሄድ ጭምር በሚሰጠው ክትባት ላይ ወላጆች ልጆቻቸውን በማስከተብ ግዴታቸውን እንደወጡ ጥሪ ያቀረቡት ደግሞ የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር አጉኔ አሾሌ ናቸው።
 
ከክትባት ዘመቻው ጎን ለጎን የወባ ወረርሽኝን ለመከላከል በማኅበረሰቡ ተሳትፎ የወባ መራቢያ ሥፍራዎችን የማጽዳትና ያቆረ ውኃን የማፋሰስ ሥራ እንደሚሠራ ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም