ቀጥታ፡

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን ሹመት አጸደቀ

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 22/2018 (ኢዜአ)፡-የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

የቦርድ አባላቱን ሹመት አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት በምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ምህረቱ ሻንቆ (ዶ/ር) ተሿሚዎቹ በትምህርት ዝግጅት እንዲሁም ባዳበሩት ክህሎት የድርጅቱን ተልእኮ ማሳካት የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ብሔራዊ ጥቅምን መረዳት የሚችሉ እንዲሁም ተቋሙን ለስኬት እንደሚያበቁ የታመነባቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።

በዚህም ፦

1፡- ብሌን ማሞ ....... የቦርድ ሰብሳቢ

2፡- ፈዲላ ቢያ ....... አባል

3፡- ተስፋዬ ዘውዴ ....... አባል

4፡- መሐመድ ካሳ ....... አባል

5፡- አፈወርቅ በደዊ ....... አባል

6፡- አስማ ረዲ ....... አባል

7፡- ዮናስ በቀለ ....... አባል

8፡- ሃፍታይ ገብረእግዚአብሔር ....... አባል

9፡- ኢሳያስ ካሳ (ዶ/ር)....... አባል ሆነው እንዲሾሙ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ምክር ቤቱ መርምሮ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

ተሿሚዎችም በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ-መሀላ ፈጽመዋል።

#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም