ቀጥታ፡

ቅርሶችን በማልማት የቱሪስት ፍሰቱን በመጨመር ተጠቃሚነትን ማሳደግ ተችሏል

ደብረ ማርቆስ፤ ሚያዝያ 22/2018 (ኢዜአ)፡- ተፈጥሮአዊና ሰው ሠራሽ ቅርሶችን በማልማት ኢኮኖሚያዊ  ተጠቃሚነትን ማሳደግ መቻሉን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዞኑ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አስታውቋል።

መንግሥት ከ18 ሚሊየን ብር በላይ በጀት መድቦ ሕብረተሰቡን በማሳተፍ የመስኅብ ልማት ማከናወኑን የመምሪያው ኃላፊ ብርቄ ይዘንጋው ለኢዜአ ተናግረዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራትም ከ160 ሺህ በላይ ቱሪስቶች በዞኑ ጉበኝት ማድረጋቸውን ጠቁመው፤ ከዚህም ከ46 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም