ቀጥታ፡

አትሌቲኮ ማድሪድ እና አርሰናል አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 22/2018 (ኢዜአ)፡- በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ መርሐ ግብር አትሌቲኮ ማድሪድ እና አርሰናል ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

 

በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቪክቶር ዮኮሬሽ በ44ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠረው ጎል አርሰናል መሪ ሆኗል።

ከእረፍት መልስ ሁሊያን አልቫሬዝ በ56ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት አትሌቲኮን አቻ አድርጓል።

 

በ78ኛው ደቂቃ ኤበሬቺ ኤዘ ላይ በተፈጸመ ጥፋት አርሰናል ያገኘው የፍጹም ቅጣት በቪዲዮ በታገዘ ዳኝነት (ቫር) ታይቶ ተሽሯል።

የፍጹም ቅጣት ምቱ ውሳኔ መቀልበስ የአርሰናል የቡድን አባላትን ያላስደሰተ ሲሆን ግልጽ የሚያሰጥ ጥፋት ነው በሚል ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ጨዋታው ተመጣጣኝ ሊባል የሚችል ፉክክር ተደርጎበታል።

የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ በቀጣዩ ሳምንት ማክሰኞ ይደረጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም