ቀጥታ፡

አዳማ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ነጥብ ተጋሩ 

አዲስ አበባ ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አዳማ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
 
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አቡበከር ሳኒ በ31ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ አዳማ ከተማ መሪ ሆኗል። 

ከእረፍት መልስ ተቀይሮ የገባው አብዱሰላም ዩሱፍ በ79ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ጎል ለድሬዳዋ ከተማ አንድ ነጥብ አስገኝታለች። 

ውጤቱን ተከትሎ አዳማ ከተማ በ34 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ዘጠኝ የሊግ  ጨዋታዎች ከድል ርቋል።

ድሬዳዋ ከተማ በ33 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች አላሸነፈም።

ዛሬ በተደረጉ የ29ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች መቻል ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0፣ ኢትዮጵያ መድን ሃዋሳ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፈዋል። 

ሸገር ከተማ እና ወላይታ ድቻ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም