ሸገር ከተማ እና ወላይታ ድቻ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ሸገር ከተማ እና ወላይታ ድቻ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሸገር ከተማ እና ወላይታ ድቻ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
ጨዋታው የተደረገው በአዲስ አበባ ስታዲየም ነው።
ውጤቱን ተከትሎ ሸገር ከተማ በ36 ነጥብ ደረጃውን ከዘጠነኛ ወደ ስምንተኛ ከፍ አድርጓል።
ወላይታ ድቻ በ35 ነጥብ ከነበረበት 11ኛ ደረጃ ወደ 10ኛ ከፍ ብሏል።