መቻል ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
መቻል ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ጋናዊው ኮሊንስ ኮፊ በ61ኛው ደቂቃ ግቧን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በሊጉ 12ኛ ድሉን ያስመዘገበው መቻል በ47 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሰባት ዝቅ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ42 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ቡድኑ ባለፉት ሁለት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።