ቀጥታ፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 18ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ 6ኛው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ 18ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ እንደሚያኪድ ተገለጸ።

ምክር ቤቱ 18ኛ መደበኛ ስብሰባውን በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥትና በሴራሊዮን ሪፐብሊክ፤ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት እና በአንጎላ ሪፐብሊክ፤ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት እና በባንግላዲሽ ሕዝባዊ ረፐብሊክ እንዲሁም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት እና በኢስዋቲኒ ንጉሠ ነገሥት መንግሥታት መካከል የተደረገውን የአየር አገልግሎት ስምምነት ለማጽደቅ የቀረቡ አራት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራም ተመላክቷል።

በሌላ በኩል ምክር ቤቱ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት እና በሩሲያ ፌዴሬሽን መካከል የጋራ የባዮሎጂ ምርምር ማዕከል ለማቋቋም የተፈረመውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራም እንዲሁ።

በመጨረሻ ምክር ቤቱ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት እና በቬትናም ሶሻሊስት ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል የዲፕሎማቲክ ወይም ኦፊሻል የአገልግሎት ፓስፖርት ለያዙ ሰዎች ቪዛን ለማስቀረት የተፈረመውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን ሹመት መርምሮ እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም