ቀጥታ፡

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን ከወራጅ ቀጠና የወጣበትን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አገኘ 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ሃዋሳ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ተባረክ ሄፋሞ በሰባተኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ሃዋሳ መሪ ሆኗል።

አማኑኤል ኤርቦ በ17 እና በ79ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋቸው ጎሎች ለመድን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አስገኝተዋል።

ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኢትዮጵያ መድን በ34 ነጥብ ደረጃውን ከ17ኛ ወደ 12ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።

የወቅቱ የዋንጫ ባለቤት የሆነው መድን በሊጉ ሰባተኛ ድሉን አስመዝግቧል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሃዋሳ ከተማ በ43 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።

ሃዋሳ ከተማ ባለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች ከድል ርቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም