በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ባህር ዳር ከተማ ወሳኝ ድል አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ባህር ዳር ከተማ ወሳኝ ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አስቴር ደግአረገ እና ምህረት ታፈሰ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
የባህር ዳር ከተማዋ ወርቅነሽ መለሰ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
በሊጉ ስድስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ባህር ዳር ከተማ በ19 ነጥብ ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ 10ኛ ከፍ ብሏል። ከወራጅ ቀጠና ስፍራ የራቀበትን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።
በውድድር ዓመቱ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዳማ ከተማ በ21 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ቡድኑ ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።
ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ የ23ኛ ሳምንት ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 0 ረቷል።