ሃዋሳ ከተማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
ሃዋሳ ከተማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ሃዋሳ ከተማ አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብርቱካን ገብረክርስቶስ እና የምስራች ላቀው ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ከሁለት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሃዋሳ ከተማ በ46 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ደረጃ ከፍ አድርጓል። በሊጉ 13ኛ ድሉንም አሳክቷል።
በውድድር ዓመቱ 17ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በ10 ነጥብ የመጨረሻውን 14ኛ ደረጃን ይዟል።
ቡድኑ ባለፉት 16 የሊግ ጨዋታዎች ከድል የራቀ ሲሆን የመውረዱ ነገር እርግጥ እየሆነ የመጣ ይመስላል።