ዘጠኝ ጎሎች በተቆጠሩበት አዝናኝ ፍልሚያ ፒኤስጂ ባየር ሙኒክን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
ዘጠኝ ጎሎች በተቆጠሩበት አዝናኝ ፍልሚያ ፒኤስጂ ባየር ሙኒክን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ፒኤስጂ ባየር ሙኒክን 5 ለ 4 አሸንፏል።
በፓርክ ደ ፕራንስ በተካሄደው ጨዋታ ክቪቻ ክቫራትስኬሊያ እና ኡስማን ዴምቤሌ በተመሳሳይ ሁለት ጎሎችን አስቆጥረዋል።
ጆአኦ ኔቬስ ቀሪዋን ጎል ለፈረንሳዩ ቡድን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ሃሪ ኬን፣ ሉዊስ ዲያዝ፣ ማይክል ኦሊሴ እና ዳዮት ኡፓሜካኖ ለባየር ሙኒክ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ጨዋታው እጅግ አዝናኝ፣ ሳቢ፣ በርካታ የግብ እድሎች የተፈጠሩበት እና በማጥቃት ላይ የተመሰረተ ነበር።
ሁለቱም ቡድኖች ተጨማሪ ጎሎችን ማስቆጠር የሚችሉባቸውን እድሎች አልተጠቀሙም።
ጨዋታው "ከፍጻሜው በፊት የተደረገ የፍጻሜ ጨዋታ" የሚል ስያሜ አግኝቷል።
ፒኤስጂ ጨዋታውን ቢያሸንፍም ለፍጻሜው የሚያልፈው ቡድን የመልስ ጨዋታው ይወስነዋል።
የኃያላኑ የመልስ ጨዋታ በቀጣይ ሳምንት ረቡዕ የሚደረግ ይሆናል።