ቀጥታ፡

ሸገር ከተማ ወደ አሸናፊነት ተመለሰ 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሸገር ከተማ ሲዳማ ቡናን 4 ለ 1 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዓይናለም ዓለማየሁ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርታለች።

ማርታ ወልዴ ቀሪዋን ጎል ለሸገር ከተማ ከመረብ ላይ አሳርፋለች።

ምትኬ ብርሃኑ ለሲዳማ ቡና ብቸኛውን ግብ  አስቆጥራለች። 

ሀትሪክ የሰራችው ዓይናለም አለማየሁ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።

ከአራት ተከታታይ የአቻ ውጤቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሸገር ከተማ በ44 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉም 13ኛ ድሉን አስመዝግቧል።

በውድድር ዓመቱ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና በ31 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

ዛሬ በተደረገ የ23ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ መቻል ልደታ ክፍለ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም