ቀጥታ፡

መቻል ወሳኝ ድል አሳክቷል 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ መቻል ልደታ ክፍለ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ገነት ኃይሉ እና ቱሪስት ለማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ግብ ያስቆጠረችው ገነት ኃይሉ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።

ውጤቱን ተከትሎ በሊጉ 15ኛ ድሉን ያስመዘገበው መቻል በ51 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት ዝቅ አድርጓል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 14ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ልደታ ክፍለ ከተማ በ19 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም