የበጋ መስኖ እርሻ በምግብ ራሳችንን ለመቻል በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የጸና መሰረትን የጣልንበት ምዕራፍ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የበጋ መስኖ እርሻ በምግብ ራሳችንን ለመቻል በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የጸና መሰረትን የጣልንበት ምዕራፍ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018 (ኢዜአ)፡- የበጋ መስኖ እርሻ በምግብ ራሳችንን ለመቻል በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የጸና መሰረትን የጣልንበት ምዕራፍ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የውሃ ሀብታችንን በአግባቡ በመጠቀም፣ ባልተቋረጠ ጥረት እና ቁርጠኝነት፣ የመልማት ጉዟችን አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ የምግብ ዋስትና ወደምናረጋግጥበት ብሩህ ተስፋ እንደሚያሸጋግረን ጥርጥር የለውም ብለዋል።