ቀጥታ፡

የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶችን በሁሉም ወረዳዎች ተደራሸ ለማድረግ ትኩረት ተደርጓል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018 (ኢዜአ)፡- በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ወረዳዎች የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶችን ተደራሸ ለማድረግ ትኩረት መደረጉን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አስታወቁ።

የትምህርት ሚኒስቴር የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ከሁሉም ክልሎችና ከድሬዳዋ አስተዳደር ጋር በጋራ ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት አድርጓል። 
 
ሚኒስትሩ በስምምነት መርሐ-ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ በ2019 የትምህርት ዘመን በሁሉም ወረዳዎች የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶችን ተደራሸ ለማድረግ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ ይገኛል። 
 
ስምምነቱም ሚኒስቴሩና ክልሎች በጋራ 1 ሺህ 452 ቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶችን እንዲገነቡ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። 
 
የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚጀመርም ጠቁመዋል።

በቀጣዩ ዓመትም ትምህርት ቤቶቹ ወደ አገልግሎት እንደሚገቡ ተናግረዋል።

ይህም የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤት የሌለው ወረዳ እንዳይኖርና የቅድመ አንደኛ ትምህርትን ተደራሸነት ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ነው በአጽንኦት የገለጹት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም