ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይከናወናሉ።

የዕለቱ ቀዳሚ ጨዋታ ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ በልደታ ክፍለ ከተማ እና በመቻል መካከል ይካሄዳል።

ልደታ ክፍለ ከተማ በ19 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል። መቻል በ48 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

በ22ኛ ሳምንት ከሸገር ከተማ ሁለት አቻ የተለያየው ልደታ ክፍለ ከተማ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል።

በተመሳሳይ በ22ኛ ሳምንት አዳማ ከተማን 2 ለ 0 የረታው መቻል ካሸነፈ ተከታታይ ድሉን ያስመዘግባል።

በሌላኛው መርሐ ግብር ሸገር ከተማ ከሲዳማ ቡና ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ በ41 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። ሲዳማ ቡና በ31 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በ22ኛ ሸገር ከተማ በ22ኛ ሳምንት ከልደታ ክፍለ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ ሁለት አቻ ሲለያይ ሲዳማ ቡና ሃዋሳ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።

ጨዋታው ሸገር ከተማ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ፣ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ድላቸውን ለማስመዝገብ የሚያደርጉት ነው።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት እስከ ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። 

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሊጉን በ54 ነጥብ እየመራ ነው።

በከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ደረጃ የኢትዮ ኤሌክትሪኳ ዳግማዊት ሰለሞን በ23 ግቦች ቀዳሚ ስትሆን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ ረድኤት አስረሳኸኝ በ16 ግቦች ትከተላለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም