አቶ አገኘሁ ተሻገር በቀድሞው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አምባሳደር ያለው አባተ ኅልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
አቶ አገኘሁ ተሻገር በቀድሞው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አምባሳደር ያለው አባተ ኅልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2018 (ኢዜአ) :- የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በቀድሞው የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አምባሳደር ያለው አባተ ኅልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በራሳቸው እና በምክር ቤቱ ስም ገልጸዋል።
የቀድሞ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አምባሳደር ያለው አባተ ባደረባቸው ሕመም ሕክምና ሲደረግላቸው ቆይተው ዛሬ ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ሕይወታቸው አልፏል።
አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በሀዘን መግለጫ መልዕክታቸው፥ አምባሳደር ያለው አባተ ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳይሉ ለሀገራቸው የሰጡት አገልግሎት እና የላቀ አስተዋጽኦ ሁሌም በክብር የሚታወስ ነው ብለዋል።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው ሁሉ ፈጣሪ መጽናናቱን እንዲሰጣቸው ከልብ እመኛለሁ ሲሉም ሀዘናቸውን ገልፀዋል።